የኮሚሽነር ጄኔራል መልዕክት

Commissioner Image

የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

በቅድሚያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለሀገራችን የፖሊስ አባላት እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልኩ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መላውን ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ በአዲስ ዓመት ካለፈው የተሻለ አንፀባራቂ ውጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋና የተቋማችንን ከፍታ የሚያረጋግጥበት ዘመን እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።

ዝርዝር መልዕክት

አዳዲስ ዜናዎች!

 • የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት( Commissioner Message)

  የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

  በቅድሚያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለሀገራችን የፖሊስ አባላት እንኳን ለ2015 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልኩ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መላውን ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ በአዲስ ዓመት ካለፈው የተሻለ አንፀባራቂ ውጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብሩህ ተስፋና የተቋማችንን ከፍታ የሚያረጋግጥበት ዘመን እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።

 • ከ44 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይት ተያዘ( Federal News)

  ጎንደር ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ):- መነሻውን ሁመራ በማድረግ ወደ ማዕከላዊ ጎንደር በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ44 ሺህ በላይ የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

  ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማሰራጨት ሁከት ለመፍጠር የሚጥሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሙከራቸው በየጊዜው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ጠንካራ ክትትል እየከሸፈባቸው ይገኛል፡፡

 • የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ በኮልፌ ልዩ ልዩ ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ችግኝ ተከላ አካሄደ( Federal News)

  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡- የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በመቀናጀት በኮልፌ ልዩ ልዩ ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሀገራዊ መርሀ ግብሩን ተከትለው የችግኝ ተከላ አካሂዷል።

  “ችግኝ ተክዬ ሳንባዬን አድሳለሁ፤ በችግኙ የዝናብ ጠብታ ግድቤን እሞላለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት የችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ችግኝ በመትከል ንግግር ያደረጉት ክቡር ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ ችግኝ ተክለን ሀገራችንን አረንጓዴ የማልበስ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነና አመርቂ ውጤትም እየተመዘገበ እንደሆነ ተናግረው አመቺውን የክረምት ወቅት በመጠበቅ ችግኝ መትከል ለሀገራችን ልማትና ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

 • የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር መመሪያን አፅድቆ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ( Federal News)

  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፦ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት አዋጁን ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪያ አስተዳደር አጠቃቀም እና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 02/2014 አጽድቆ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ።

  ይህ መመሪያ የዳኝነት አካሉ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጁ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ ለመስጠት ግልጽ እና ዝርዝር ጉዳዮችን ተመልክቶ በተቀራራቢና ተመሳሳይ የወንጀል ጉዳዮች መካከል ተቀራራቢነት ያለው ቅጣት እንዲወሰን ለማድረግ እንዲሁም እንደ ወንጀሉ ክብደትና አደገኛነት የቅጣት ተመጣጣኝነት ማረጋገጥን ግብ አድርጎ የወጣ ነው፡፡

 • ሁለት የዲያስፖራ ማህበራት ለኢትዩጵያ ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና መሣሪዎችን በስጦታ አበረከቱ( Federal News)

  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 03 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡- ደራሽ ለኢትዩጵያ ሰሜን አሜሪካ ዲያስፖራ ማህበር ከሰርቭ ግሎባል ማህበር ጋር በመተባበር ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የህክምና መሣሪያዎችን ለኢትዩጵያ ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በስጦታ አበረከቱ፡፡

  የኢትዩጵያ ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ጤና አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ዶ/ር ደረጀ ተካልኝ ሠራዊቱ ሕግ ለማስከበር ለሀገር እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት በመገንዘብ የዲያስፖራው ማህበረሰብ በጤናው ዘርፍ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ከአሁን በፊትም ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ጠቅሰው አሁንም ሁለቱ ማህበራት ሁለት ዘመናዊ 4D ኤክስሬይ አልትራ ሳውንድ እና ለቀዶ ጥገና ህክምና የሚያገለግል ላፓራስ ኮፒ ማሽን ለኢትዩጵያ ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ማበርከታቸውን ገልፀው የተበረከቱ የህክምና መሣሪያዎችም እጅግ ጠቃሚና ችግር ፈቺ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 • በሻሸመኔ ከተማ 122 ኩንታል አደገኛ ዕፅ ተይዞ ተወገደ( Regional News)

  ሻሸመኔ፣ ነሐሴ 02 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡- የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና ከሌሎች ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት 122 ኩንታል አደገኛ ዕፅ ይዞ ማስወገዱን ገለፀ።

  የሻሽመኔ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሽመልስ ቀናው በወረዳው ውስጥ አደገኛ ዕፅ ለመቆጣጠር ተከታታይ የፓትሮል ቅኝትና ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ቤት ለቤት በተደረገው ድንገተኛ ብርበራና ፍተሻ አደንዛዥ ዕፁንና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደተቻለ ተናግረዋል።

የሚሰጡ አገልግሎቶች

ወንጀል መከላከል


የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን ይጠብቃል፤ ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ለውጭ አገር የክብር እንግዶችና ዲፕሎማቶች ጥበቃ ያደርጋል፤


አስተዳደርና ልማት


በፖሊስ ምልመላና ቅጥር፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በማዕረግ አሰጣጥ፣ በደንብ ልብስ አለባበስ፣ በትጥቅና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ሀገር አቀፍ ደረጃዎችን ያወጣል፤


ወንጀል ምርመራ


የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፍትሕ ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በጋራ ይሠራል፤


ወንጀል መከላከል


በሕገ-መንግሥቱና ሌሎች ህጎችን፣ በመንግሥትና በሀገር ፀጥታ እና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚፈፀሙ ማናቸውም ዓይነት የወንጀል ስጋቶችና ድርጊቶችን ይከላከላል፡፡