ወንጀል መከላከል


ዳይሬክተሩ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅን ማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዋና ምክንያት ሲገልፁ የወንጀል መከላከል ስራ በተለይም የፖሊስ፣የአቃቢ ህግ ወይም የፀጥታ አካላት ስራ ብቻ አድርጎ የሚተዉ አይደለም የሁሉም ባለሙያ ሀላፊነት ነዉ ካሉ በኋላ ስለሆነም የፌዴራል መንግስት ወንጀልን የመከላከሉ ስራ የወንጀል መንስኤዎች እና ተስማሚ የመከላከያ እርምጃዎች ለይቶ በሚያስቀምጥ መንገድ ሊተገበርና ሊመዘን በሚችል ስትራቴጂ መመራት ስላለበት ስትራቴጅዉን ማዘጋጀት አስፈልጓል ብለዋል፡፡

የስትራቴጂው ዝርዝር አላማዎችም ለወንጀል ድርጊቶች መፈጸም ምቹ የሆኑ ሁኔታዎችን በማስወገድ እና የወንጀል መከላከል ስራን ሊያግዙ የሚችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት የወንጀል መከላከል ስራ ማከናወን፤ ለህብረተሰቡ ዋና ስጋት የሆኑ፣ ልዩ ትኩረት የሚሹና ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶችን አይነትና መንስኤዎቻቸውን በመለየት ድርጊቶቹን ለመከላከል የሚያስችሉ በመረጃና ምርጥ ተሞክሮዎች ላይ የተመሰረቱ ስልቶችን መንደፍ ነዉ ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በወንጀል መከላከል ስራ የባለድርሻና አጋር አካላትን ተግባርና ኃላፊነት በማስቀመጥ ውጤታማ የሆኑ የወንጀል መከላከል ተግባራትን ማከናወንና መከታተል የሚያስችል እና የተቀናጀ አሰራር በመካከላቸው እንዲኖር የሚያግዝ ሥርዓት መዘርጋት፤ወንጀል ጠል የሆነ ማህበረሰብ በመፍጠር እና በሕዝቦች ንቁ ተሳትፎ የዳበረ ጠንካራ የወንጀል መከላከል ሥርዓት በመዘርጋት የህግ ማስከበር ተግባርን ማጠናከር፤ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የወንጀል መከላከል ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል አቅም መፍጠርና የስትራቴጂውን አፈጻጸም የሚያስተባብር አካልን ተግባርና ኃላፊነት በማስቀመጥ ወንጀልን ከመለካለከል አንፃር ውጤታማ የሆነ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋትም የስትራቴጂዉ አላማዎች መሆናቸዉን አቶ በላይ ሁን አክለዉ ገልፀዋል፡፡

የወንጀል ስትራቴጅዉ ሲዘጋጅም ጠቅላላ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅና፣የተለዩ የወንጀል አይነቶች በሚሉ በሁለት ዋና ዋና አይነቶች ላይ ተመስርቶ እንደተዘጋጀ የገለፁት ዳይሬክተሩ በተለይም የሽብር ወንጀል፣በመሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ከባድ የኢኮኖሚና ከገንዘብ ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር ማሻገር ፣በሰላምና ፀጥታ፣በሴቶችና ህፃናትና መሰል ከ10 በላይ የሚደርሱ የወንጀል አይነቶች ላይ በመመስረትና በነዚህ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅ ተግባራት ዉስጥ ምን ምን ተግባራት ይከናወናሉ ማን ምን ይሰራል፣ማንስ ያስተባብራል የሚሉት ነገሮች በዝርዝር የተካተቱ መሆናቸዉን አክለዋል፡፡

ይህ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅ ሲሰራ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ እነዚህ ሀላፊነት የተሰጣቸዉ አካላት በተገቢዉ መንገድ ተናበዉና ተቀናጅተዉ መስራት ከቻሉ ወንጀልን መቀነስ ይቻላል ሲሉ እምነታቸዉን ተናግረዋል፡፡

አገር አቀፍ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅ በፌዴራልና በክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ዉይይት ተካሂዶበት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኳል የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ስትራቴጅዉን ተመልክቶ ካጸደቀዉ በኋላ ወደ ስራ ይገባል ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡


የወንጀል መከላከል አገልግሎት


ወንጀል መከላከል

የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን ይጠብቃል፤ ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ለውጭ አገር የክብር እንግዶችና ዲፕሎማቶች ጥበቃ ያደርጋል፤


ተጨማሪ አገልግሎቶች