31.  ለፖሊስ አባላት የሚያገለግሉ የደመወዝ ስኬል እና ልዩ ልዩ አበሎችን አጥንቶ ለመንግስትያቀርባል፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ያደርጋል፤

32.  ለሥራ ክፍሎቹና ለፖሊስ አባላት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ቢሮዎችና የመኖሪያ ካምፖች እንዲሠሩ ያደርጋል፤

33.  በከተማ ውስጥ የሚሰሩ የወንጀልና የድንገተኛ አደጋ ስጋት ይፈጥራሉ ተብለው የሚገመቱ ግንባታዎችን የሚመለከቱ ፕላኖች ለወንጀልና አደጋ መከላከሉ ተግባር አመችነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤

34.  ሀገሪቱ የሚቀርብላት ዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ጥሪ በአግባቡ ለመወጣት የሚችል የሠላም አስከባሪ ፖሊስ ያዘጋጃል፤

35.  ባለሞተር ተሽከርካሪ መንዳት የሚያስችል ሥልጠና ለፖሊስ አባላት ይሰጣል፤በአዋጅ ቁጥር 6)/2ሺ አንቀጽ 5(2)  መሠረት በትራንስፖርት ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ሲሰጠውም መንጃፈቃድ ይሰጣል፤

36.  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሚያስተዳድራቸው መንገዶች ላይ የመንገድ ትራፊክ ደንቦች መከበራቸውን ይቆጣጠራል፣ የትራፊክ አደጋዎችን ይመረምራል፤

37.  ፖሊስ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አግባብ ካላቸው የውጭ ሀገር መንግስታት ፖሊስ ተቋማትና መንግሥታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሠርታል፤

38.  ከዓለም አቀፍ ፖሊስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ ወንጀለኞችን መረጃ ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ያሰራጫል፣ ተከታትሎ ይይዛል፤   

39.   በሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች ለፌዴራል ፖሊስ የተሰጡ ሥልጣንና ተግባራትን በሥራ ላይ ያውላል፤

 ውል ይዋዋላል፣ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፡፡

Pages: 1  2  3