16.  በፎረንሲክ ምርመራ ጉዳዮች ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በቅንጅት ይሰራል፤

17.  በማስረጃነት አገልግሎት ሊሰጡ የማይችሉ የወንጀል ምርመራ መዛግብቶችን፣ ሰነዶችን፣ አሻራዎችንና ተያያዥነት ያላቸው ሪከርዶች ከብሔራዊ ቤተ -መዛግብትና ቤተ - መፃሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር እንዲወገዱ ያደርጋል፤

18.  የሽብርተኝነት ድርጊት ሊፈፀም እንደሚችል ለመጠርጠር በቂ ምክንያት ሲኖርና ድርጊቱንም ለመከላከል ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ሲታመንበት በተጠረጠረው አካባቢ የተገኙ ተሽከርካሪዎችና እግረኞችን በማስቆም ድንገተኛ ፍተሻ ያደርጋል፤  ተጠርጣሪ ሰዎችና ማስረጃዎችን በመያዝ ይመረምራል፤

19.  ከሽብርተኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ የሀገርን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመመ ርመር የሚረዳ መሆኑ የታመነበትን መረጃ ወይም ማስረጃ ከማንኛውም ሰው ጠይቆ ይወስዳል፤

20.  ተልዕኮውን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉና የፖሊስ ሙያ ብቃትና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ በሥራላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤

21.  ከክልል የፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ስለወንጀልመከላከልናምርመራሀገርአቀፍፖሊሲዎችን፣ስትራቴጂዎችንናአንድወጥየሆኑየአሠራርደረጃዎችን ያዘጋጃል፤በመንግሥትሲጸድቁምተግባራዊመደረጋቸውንያረጋግጣል፤

22.  በፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ በሚሰጠው ትእዛዝ መሠረት በክልሎች ሕግና ሥርዓትን ያስከብራል፤

23.  ስለወንጀልና ስለትራፊክ አደጋ መንስኤዎች ሀገርአቀፍ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፤

24.  ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ትኩረት በመስጠት ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች የትምህርት፣ የሙያ ሥልጠና፣ የቴክኒክ እና የምክር ድጋፍ ይሰጣል፤

25.   ለአባላቱ የሚያገለግሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንና የስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከላትን ያደራጃል፤

26.  የጦርመሳሪያወይምፈንጂለመያዝ፣ለመጠቀም፣ወደአገርውስጥለማስገባት፣ለመሸጥእናለመጠገንፈቃድይሰጣል፤ዝውውራቸውንይቆጣጠራል፤

27.  መወገድ የሚገባውን ማናቸውንም የጦር መሣሪያ ወይም ፈንጂ ያስወግዳል፤

28.   የጥበቃ አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ መሠማራት ለሚፈልጉ የግል ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤

29.  የፎረንሲክ ምርመራ አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ መሠማራት ለሚፈልጉ ሰዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤

30.  ከፀጥታ አካላት ጋር በጥናት፣ በሥልጠና እና በመረጃ ልውውጥ ረገድ በቅንጅት ይሠራል፤

Pages: 1  2  3