የኮሚሽኑ ሥልጣንናተግባር

ኮሚሽኑየሚከተሉትሥልጣንናተግባራትይኖሩታል፡-

1.    በሕገ-መንግሥቱና በሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ፣ በመንግሥትና በሀገር ፀጥታ እና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚፈፀሙ ማናቸውም ዓይነት የወንጀል ስጋቶችና ድርጊቶችን ይከላከላል፣ ይመረምራል፤

2.    የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፍትሕ ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በጋራ ይሠራል፤

3.    በፍርድ ቤቶች የሚሰጡትን ትእዛዞችና ውሳኔዎች ይፈፅማል፤

4.     በሌሎች ህጐች ለሌሎች የፌዴራል መንግሥት አካላት የተሰጠ ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክልል ስር የሚወድቁ ወንጀሎችን ይከላከላል፣ ይመረምራል፤

5.     የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡-

ሀ) የሃሰት ገንዘብና የክፍያ ሰነዶችን በመሥራት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ይከላከላል፣ ይመረምራል፤

ለ) ከመረጃ መረብና ከኮምፒዩተር ሥርዓት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ይመረምራል፤

ሐ) ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና እገታ፣ የአደገኛ ዕፆች ዝውውርና ስርጭት፣ የአውሮፕላን ወይም የመርከብ ጠለፋ፣ የተደራጀ ዘረፋ፣ ውንብድና፣ አሸባሪነት እና የፀጥታ ማደ ፍረስ ወንጀሎችን ይከላከላል፣ ይመረምራል፤

6.    አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሥር የሚወድቁ የወንጀል  ጉዳዮችን እንዲከላከሉና እንዲመረምሩለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች የውክልና ስልጣን ይሰጣል፤በውክልናውመሠረት  ስለተፈጸሙጉዳዮች ሪፖርት ይቀበላል፤

7.    በፖሊስ ምልመላና ቅጥር፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በማዕረግ አሰጣጥ፣ በደንብ ልብስ አለባበስ፣ በትጥቅና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ሀገር አቀፍ ደረጃዎችን ያወጣል፤

8.    የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ያቋቁማል፤ አባላቱ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተከታታይነት ያለው ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤ 

9.    የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን ይጠብቃል፤ ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ለውጭ አገር የክብር እንግዶችና ዲፕሎማቶች ጥበቃ ያደርጋል፤

10.  ወንጀልን ለመከላከልና ለመመርመር የሚረዱ የሲ .ሲ.ቲቪ ካሜራዎችን ተገቢ በሆኑ ቦታዎች ይተክላል፤

11.  የጉምሩክና የታክስ ሕጎችን በመተላለፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ በአዋጅ ቁጥር 5)'7 /2ሺ አንቀጽ 08 የተመለከቱትን ኃላፊነቶች ይወጣል፤

12.  የሀገሪቱን ጥቅሞች በሚነኩ ጉዳዮች ላይ በውጪ ሀገር የሚፈፀሙ ማናቸውንም ወንጀሎች ከየሀገራቱ ጋር በሚደረግ የጋራ ስምምነት መሠረት ይመረምራል፤

13.  የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ አደጋ ሲከሰትና አስቸኳይ ሁኔታ ሲፈጠር ሠላምና ፀጥታን በማስፈን የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትጋር በመቀናጀት ይሰራል፤

14.  የግለሰቦችን የወንጀል ሪከርዶች በማዕከል አደራጅቶ ይይዛል፤ የወንጀል ሪከርድ ለሌለባቸው ግለሰቦች ከወንጀል ነፃ ማስረጃ ይሰጣል፤

15.  የፎረንሲክ ምርመራ ያደርጋል፣ ስለመረመረው ጉዳይ ማስረጃ ይሰጣል፣ ለፍርድ ቤት ወይም ለጠያቂው አካል የሙያ ምስክርነት ይሰጣል፤

Pages: 1  2  3