የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተቋሙን ችግር ይፈታሉ የተባሉ 3 አውደ ጥናቶችን አቀረበ፡፡

       ነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ/ም በቀረበው አውደ ጥናት የአባላት ምልመላና ስልጠና፣የሰራተኞች የስራ ላይ እርካታ እንዲሁም በፕሮጀክት ግንባታ ላይ የሚታዩ አጠቃላይ ችግሮች የተዳሰሱ ሲሆን የችግሮቹ መንስኤዎች የበጀት ችግር፣ከማህበረሰቡ እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር አለመስራት የሚሉት በጥናቱ ተካተዋል:: ችግሮችን ለማስወገድ ብሎም ውብና ማራኪ ተቋም ለማድረግ ከተሳታፊዎች መካተት አለባቸው የተባሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ጥቆማ ተደርጎባቸዋል፡፡