በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የስፖርት ክለብ (ኦሜድላ) በ2011 ዓ.ም የተገኘ ውጤት

1)  ቦክስ ቡድን፡- በአመት ውስጥ 5 ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን ያስመዘገቡት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ብዛት ወርቅ =10፣ ብር =11፣ ነሃስ =13 ፣ ዋንጫ =2 በአገር ውስጥ በተደረገው የአመቱ የዙር ውድድር በድምሩ 34 ሜዳሊያና 2 ዋንጫዎችን አስገኝተዋል፡፡ በዚህም በአገራችን ከሚገኙ የቦክስ ክለቦች የኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን የአመቱን ውድድር ያጠናቀቁ ሲሆን አንድ አሰልጣኝና አንድ ብ ስፖርተኛ  እንዲሁም ሦስት ስፖርተኞችን ለብሔራዊ ቡድን በማስመረጥ የአመቱን ውድድር አጠናቀዋል፡፡

2)  አትሌክስ ማራቶን ቡድን፡- በአመት ውስጥ 5 ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን በዚህም ወርቅ =2፣ ብር =1፣ ነሃስ =3፣ ዋንጫ =3 የተገኘ ሲሆን፤ በአገር ውስጥ በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች በድምሩ 6 ሜዳሊያና 3 ዋንጫዎችን አስገኝተዋል፡፡ በተጨማሪ 3 ስፖርተኞችን ለብሔራዊ ቡድን አስመርጠዋል፡፡

3)  እጅ ኳስ ቡድን፡- በአመት ውስጥ 17 ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን ያስገኙት ውጤት

  • 12 ጨዋታ አሸንፈዋል
  • 6 ጨዋታ ተሸንፈው በአገር ውስጥ በተደረገው የዙር ውድድሮች 22 ነጥብ በመያዝ ከ10 ክለቦች 4ኛ ደረጃ በመሆን የአመቱን ውድድር ያጠናቀቁ ሲሆን

4)  እግር ኳስ ቡድን፡- በአመት ውስጥ 22 ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን ያስገኙት ውጤት

  • 7 ጨዋታ አሸንፈዋል
  • 7 ጨዋታ አቻ ወጥተው
  •  8 ጨዋታ ተሸንፈው በአገር ውስጥ በተደረገው የከፍተኛ ሊግ የዙር ውድድር 22 ጨዋታዎችን አድርገው በአጠቃላይ 28 ነጥብ በመያዝ በሀገራችን ከሚገኙ 12 ክለቦች 5ኛ ደረጃ በማግኘት የዓመቱን ውድድር አጠናቀዋል፡፡

5)  አትሌቲክስ ረዥም ርቀት ቡድን፡- በአመት ውስጥ 7 ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን  ወርቅ =2ብር =1፣  በድምሩ 3 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የዓመቱን ውድድር አጠናቀዋል።

            የስፖርት ክለባችን በሁሉም  የስፖርት ዲስፕሊኖች አምና ከነበረው ውጤት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ውጤት በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አለን እያልን። ክለባችንን በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት በማግኘት ወደ ቀድሞ ገናና ስሙ እንዲመለስ የሁላችንም ድጋፍና ጥረት ይጠይቃል፡፡

   የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፌ/ፖ/ኮ/ህዝብ ግን/ሙ/ቲያ/ስፖርት ዳይሬክቶሬት