የፌደራል ፖሊስ አባላት መብት ለማስጠበቅ ተቋሙ ከምንግዜውም በተሻለ መልኩ ህጋዊ አሰራሮችን ተከትሎ እንደሚሰራ ተገለፀ

        የፌደራል ፖሊስ አባላት በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከአካል እስከ ህይወት መስዋእትነት በመክፈል የበኩላቸውን ሚና ሲወጡ ቆይተዋል፡፡የዘውትር ተግባራቸው የህዝባቸውና የሀገሪቱን ሰላም ማስቀጠል የሆነው የፌደራል ፖሊስ አባላት ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ጊዜ የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ 


       በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህግ ጉዳዮች እና ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ እንደተናገሩት አባላቱ ህግና ስርዓቱን ተከትለዉ ግዳጃቸውን ሲወጡ በሚፈጠሩ አንዳንድ ክፍተቶች ዙሪያ በተቋሙ የህግ ከለላ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል፡፡እንደ ኮማንደር ፋሲል ገለፃ የሰራዊቱ አባላት ወደ መደበኛ ስራቸው ከመቀላቀላቸው በፊት የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ  መብቶች እንዲያከብሩ የሚረዱ የተለያዩ የንቃተ-ህግ ስልጠናዎችና ትምህርቶች ይሰጣቸዋል፡፡በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህጋዊ አሰራሮች እንዲሰፍኑ እና የአባላቱ መብት እንዲጠበቅም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Statement on Current Issues Part-2

More Video

የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት

        የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።ይህንን ለውጥ ከግብ ለማድረስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ህገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ በቂ ዝግጅት አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

        የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የሕዝብን ደህንነት ማስከበር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተግባር ከግብ ለማድረስ ኮሚሽኑ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Pages: 1  2  3  

Follow us on Social Networks Follow us on Social Networks