የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተቋሙ ለሚሰሩ ሲቪል ሰራተኞች የማበረታቻና የዕውቅና ሽልማት አደረገ፡፡

              በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሚሰሩ 1214 የሲቪል ሰራተኞችና አመራሮች የሚገኙ  ሲሆን የ2011 ዓ/ም ዕቅድ አፈፃፀምን መሰረት በማድረግ ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ/ም ለ264 የሲቪል ሰራተኞች የገንዘብና የእውቅና ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡ከተሸላሚዎች ውስጥም 174 ሴት ሰራተኞች ሲሆኑ 90ዎቹ ደግሞ ወንድ ሰራተኞች ናቸው፡፡ከነዚህም ውስጥ 56 ሰራተኞች የ1ኛ ደረጃ፣90 ሰራተኞች የ2ኛ ደረጃ፣118 ሰራተኞች የ3ኛ ደረጃ ተሸላሚ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

            ፕሮግራሙ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ሃላፊዎችና አባሎች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ም/ኮሚሽነር ጀነራል ይህደጎ ስዩም የተቋሙ እቅድ ውጤታማ እንዲሆን የሌሎች አባሎች ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ የሲቪል ሰራተኞች ሚና የማይተካ በመሆኑ ወደፊት መሰል ሽልማቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ በእለቱም ሊነጋ ሲል የተሰኘው ሙዚቃዊ ተውኔት ለተመልካች ቀርቧል፡፡

           የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ሽልማቶችና እውቅና መስጠቱ የሚቀጥል በመሆኑ ለበለጠ ውጤት ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Audio List
Statement on Current Issues Part-2

More Video

የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት

        የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።ይህንን ለውጥ ከግብ ለማድረስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ህገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ በቂ ዝግጅት አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

        የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የሕዝብን ደህንነት ማስከበር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተግባር ከግብ ለማድረስ ኮሚሽኑ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Pages: 1  2  3  

Follow us on Social Networks Follow us on Social Networks