የቻይናው የምድር ባቡር ፖሊስ ኮሌጅና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

             የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከተቋቋመ ከ1939 ዓ/ም ጀምሮ የተለያዩ ፖሊሳዊ ስልጠናዎችን በሀገራችን ብሎም በጎረቤት ሀገራት በማሰልጠን የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አገልግሎቱን የበለጠ ለማሳደግ እ.ኤ.አ በ1950  ከተመሰረተው ከቻይናው የምድር ባቡር ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በምድር ባቡር ጥበቃና ደህንነት ላይ አብረው የሚሰሩበትን የሁለትዮሽ ስምምነት ሀምሌ 5 ቀን 2011 ዓ/ም አድርገዋል፡፡

          በስምምነቱም የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሰው ሀይል ስልጠና ከቻይናው የምድር ባቡር ፖሊስ ኮሌጅ ጋር የሚደረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ከቀድሞው የተለየ የምድር ባቡር ጥበቃና ደህንነትን የሚከታተል የምድር ባቡር ደቪዥን እንደሚቋቋም ተገልጿል፡፡ስምምነቱን ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት አቶ መስፍን አበበ እና የቻይናው የምድር ባቡር ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ፕሬዘዳንት ረ/ፕሮፌሰር ፒንግ ሊቭ ናቸው፡፡

Statement on Current Issues Part-2

More Video

የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት

        የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።ይህንን ለውጥ ከግብ ለማድረስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ህገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ በቂ ዝግጅት አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

        የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የሕዝብን ደህንነት ማስከበር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተግባር ከግብ ለማድረስ ኮሚሽኑ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Pages: 1  2  3  

Follow us on Social Networks Follow us on Social Networks