ወረርሽኝ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ለመከላከያ ሰራዊትና ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና ባለሙያዎች ተሰጠ

            ከመከከያ ሰራዊትና ከፌደራል ፖሊስ ከተለያዩ ክፍሎች ለተጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የወረርሽኝ በሽታዎች ቀድሞ በመተንበይ በመተንተንና በማስላት በተቀናጀ መልኩ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያግዝ ስልጠና እንደነበር ተነግሯል፡፡ እኝህ 57 የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም 53 የመከከያ ሰራዊት በድምሩ 110 ልጣኞች የተሳተፉበት ስልጠና ለሶስት ወር ያህል በተከታታይ በሚገባ ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡


          ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ ስልጠና የጤና ሚንስቴር የመከላከያ ሰራዊት ጤና ዋና መምሪያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና አገልግሎትና የአለም የጤና ድርጅት ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለጋራ ያዘጋጁት ነበር ነው የተባለው፡፡ሰልጣኞቹ ከስልጠናው ፈርጀ ብዙ ፋይዳ እንዳገኙ በመጥቀስ የወረርሽኝ በሽታ በአጋጣሚ ቢከሰት እንኳን ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት እንዴት በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችሉ ከፍ ምድ አዳብረንበታል ብለዋል፡፡


         ምክትል ኮማንደር አበበ ደመቀ ስልጠናው በታዊ ለሆኑ የወረርሽኝ በሽታዎችን እልባት ለመስጠት በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ከፍተኛ ልምድ ያዳበረ፤ ክህሎታቸውን የጨመረ ነበር ብለዋል፡፡በተለይ አብዛኛ የሰራዊት አባል በካ ተጠርንፎ የሚኖሩ ስለሆነ ለበሽታዎች ተጋላጭ ከመሆናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ጨምረው ተናግረዋል፡፡


   ሌላው ሰልጣኝ ሳጅን ዱሜሳ በኛ በመቐለ ከተማ የፌደራል ፖሊስ ክሊኒክን እንደምሳሌ በማንሳት የመመረቂያ ፅሁፍ ያቀረበ ሲሆን በሽታዎች አንዴ ከተከሰቱ ከፍተኛ ኪሳራ ስለሚያስከ ቀድሞ መከላከልና ጥንቃቄ ማድረጉ አማራጭ የሌለው ብቸኛው ዘዴ መሆኑ አሳይቷል፡፡ ብርጋዴል ጀነራል ዳዲ አስፋው በሽታ ከተከሰተ በኃላ ከማከም ይልቅ ቀድሞ በመከላከል ላይ ያተኮረ ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡ ሰልጣኞችም ወደየ ምድብ ቦታችሁ ስትሔዱ የተማራችሁትን ወደ ተግባር በመለወጥ ሙያዊ ግዴታችሁን በመወጣት እያንዳንዳችሁ የጤና ካድሪ ልትሆኑ ይገባል ሲሉ ዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡

Statement on Current Issues Part-2

More Video

የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት

        የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።ይህንን ለውጥ ከግብ ለማድረስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ህገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ በቂ ዝግጅት አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

        የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የሕዝብን ደህንነት ማስከበር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተግባር ከግብ ለማድረስ ኮሚሽኑ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Pages: 1  2  3  

Follow us on Social Networks Follow us on Social Networks