ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ ከሚያዚያ 14 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ ተገልጋዮችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

         የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ ከሚያዚያ 14 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ ተገልጋዮችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡


      ተቋርጦ የነበረው ጉዞ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የጋራ ስምምነት በተደረሰባቸው 3 ሃገራት ማለትም ሳውዲ አረቢያ፤ጆርዳን እና ኳታር የሚሄዱ ተገልጋዮችን ተቀብለው እያስተናገዱ መሆናቸውን የአሻራ ምርመራ ዲቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ተፈሪ አርጋው ገልፀዋል፡፡ኮማንደሩ አክለውም ተገልጋዮች ወደ አሻራ ምርመራ ሲመጡ የታደሰ ፓስፖርት፤የህጋዊ ኤጀንሲ ደብዳቤ፤ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ እና አስር የኢትዮጵያ ብር በመያዝ በስራ ሰዓት የሚስተናገዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Statement on Current Issues Part-2

More Video

የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት የክቡር ኮሚሽነር ጀነራል መልዕክት

        የተከበራችሁ ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ፖሊሶችና አጋር የፀጥታ አካላት፣ የተከበራችሁ መላው የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።ይህንን ለውጥ ከግብ ለማድረስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ዜጎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በህግ የተሰጠውን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ህገመንግስቱንና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ በቂ ዝግጅት አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

        የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን የሕዝብን ደህንነት ማስከበር የኮሚሽኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ይህን ተግባር ከግብ ለማድረስ ኮሚሽኑ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ ነው።

Pages: 1  2  3  

Follow us on Social Networks Follow us on Social Networks